Tegbareid.jpg

PRESS RELEASE

Graduation Ceremony of SMU 2021 Undergraduate Students

 

St. Mary’s University is one of the pioneer private universities in Ethiopia. It has been contributing its share to help Ethiopia have human capital equipped with the requisite knowledge and skills which will help boost the economy. 

 

The University will mark the graduation of its 2021Undergraduate Program students on October 9,2021 (Meskerem 29, 2014E.C.) in the morning, starting at 08:30 AM, at Addis Ababa Golf Club. This year, the University will graduate a total of 1585 Undergraduate Program students (614 male and 971 female), where female students comprise 61 percent of the graduates. This shows that female participation at SMU is encouraging.

 

The ceremony will take place in the presence of the Guest of Honor Ato Biniyam Belete, Founder and Manager of Mekedonia Charity Association, and at the event Medals and Trophies will be awarded to graduates with the highest scores. 

 

St. Mary’s University would like to congratulate the graduates who made it to this day to celebrate their achievements. SMU wishes you bright future ahead. 

 

For further information, please call,

  • W/roAsnakech G/Selassie, Director, International Relations and Communication Office, St. Mary’s University.

Tel.: 011 558 06 16 (Office)

 



ጋዜጣዊ መግለጫ

 

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ የ2013ዓ.ም. የተማሪዎች የምረቃ በዓል

 

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ በአገራችን ከሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንጋፋና ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ብቃትና ጥራት ያለው የተማረ የሰው ሃይል በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አሰልጥኖ የሚያወጣ ተቋም ነው፡፡ ዩኒቨርስቲው በመደበኛው የቅድመ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን በመከታተል በመጀመሪያ ዲግሪ ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ ያስመርቃል፡፡ 

ዩኒቨርስቲው በዚህ ዓመት በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛና በማታው የትምህርት መርሃግብር 614 ወንዶችና 971 ሴቶች በድምሩ 1585 ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ ይህም በተቋሙ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ አበረታች መሆኑን ያሳያል፡፡

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ አቶ ብንያም በለጠ፣ የመቄዶንያ በጎአድራጎት ማህበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ በክብር እንግድነት የሚገኙ ሲሆን በዕለቱ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች የዋንጫና ሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የሥራ መመሪያና ምክር በክብር እንግዳው የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 

የዘንድሮው ዓመት ተመራቂዎች ለዚህ የምረቃ ቀን በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ መጪው ጊዜ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ፡-

  • ለአለም አቀፍ ግንኙነትና ኮሙኒኬን ቢሮ
  • /ሮ አስናቀች ገ/ሥላሴ ስ.ቁ.0115 58 06 16 መደወል ቻላል፡፡